የጎንደር ብቅል የተ.የግል. ማህበር የተለያየ መጠን ያላቸውን ከረጢቶች በቋሚነት ለአንድ አመት በጥራት አምርቶ የሚያቀርብለት ኩባንያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ቁጥር ጎብፋ/003/2026

ጨረታ ማስታወቂያ

የጎንደር ብቅል የተ.የግል. ማህበር በዋናነት ለሚያመርተው ብቅል እና ተረፈ ምርቶች መያዣነት የሚያገለግል የተለያየ መጠን ያላቸውን ከረጢቶች በቋሚነት ለአንድ አመት በጥራት አምርቶ የሚያቀርብለት ኩባንያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት በጥንቃቄ አንብባችሁ በጨረታ ማጠናቀቂያው ቀን ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን እንድታስገቡ እንጋብዛለን፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች -

  1. ንግድ ፈቃዱ የታደሰና ከረጢት በማምረት ስራ የተሰማራ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማያያዝ
  3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ አገልግሎት መስጫ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 500,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በጎንደር ብቅል ፋብሪካ ግዥ ክፍል ቢሮ 15/04/2026 እስከ 8/05/2026 ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. የምርት ማስረከቢያ ቦታው ጎንደር እንደመሆኑ መጠን የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስና ትራንስፖርት ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ተጫራቾች በራሳቸው ችግር ባይገኙም በተገኙት ተጫራቾች ፊት በጎንደር ብቅል ፋብሪካ ንግድ መምሪያ 8/05/2026 ከረፋዱ በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ 5፡10 ይከፈታል፡፡
  6. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በተነገረው 5 ቀናት ውሥጥ ከፋብሪካው ጋር ውል መውስድ ይኖርበታል፡፡
  7. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. መሟላት የሚገባቸውን ሰነዶች (የንግድ ፈቃድ፣የዘመኑን ግብር የተከፈለበት መረጃ እና ሲፒኦና ሌሎችን መስፈርቶች ካልተሟሉ ውድቅ ይደረጋል ፣ናሙና በፋብሪካው ግዥ ክፍል ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. ለተጨማሪመረጃ በስልክ ቁጥር፡-05 82 11 12 34/09 13 59 85 63/09 18 06 41 75/09 30 00 11 10 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የጎንደር ብቅል ፋብሪካ ኃ.የተ.የግ.ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-08
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): 8/05/2026 ከረፋዱ በ5፡00
  • Bid opening: 2026-05-08 11:10
  • Bid opening (note): 8/05/2026 ከረፋዱ በ5፡10
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Gondar Malt Factory PLC
  • Bid bond: 500,000.00 ብር
  • Published: Apr 17, 2026
  • Posted at: 2026-04-17T08:01:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders