በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሠረተ ልማት ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሚያሠራው የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ለማስገንባት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 06/18

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሚያሠራው የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ለማስገንባት ስለፈለጉ ግንባታውን ለማሠራት ያስችል ዘንድ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ነጋዴዎች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፤-

ስለዚህ ተጫራቾች -

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማስረጃ ያላቸው

3. የግዥው መጠን ብር 200,000 / ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርነት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የግንባታውን አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊክሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ከግዥ /ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይችላሉ።

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሐሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 21ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

10. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) በግዥ ፈፃሚው መሥሪያ ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጪ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።

12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0973 807 293 / 0948 088 732 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት

ቱለፋ

አድራሻ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ከፍቼ ከተማ አለፍ ብሎ እንገኛለን።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-07
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣባት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-07 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣባት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Bulga City Administration Finance Office
  • Bid bond: 1.5%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 17, 2026
  • Posted at: 2026-04-17T08:21:00.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders