ጉምቢ እህል ድርጅት በአሁኑ ወቅት በእጁ የሚገኘውን የ2017/18 ምርት ዘመን በ2018 የተገዛዉን ምርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የእህል ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 2/2018
ጉምቢ እህል ድርጅት (Dhabbata Gumbii Midhaanii) በቅርቡ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፣ በOSF፣ ተመስርቶ ወደ ስራ የገባ ድርጅት ሲሆን፤ ዋና ዓላማውም የአርሶ አደሩን ምርት በመረከብና በማከማቸት፣ ምርቱን ለሚያቀነባብሩ ድርጅቶችና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በማቅረብ የገበያ መረጋጋትን መፍጠር ነው። ድርጅታችን በአሁኑ ወቅት በእጁ የሚገኘውን የ2017/18 ምርት ዘመን በ2018 የተገዛዉን ምርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የሚሸጠው የምርት ዓይነትና መጠን፦
- ስንዴ (Wheat): 110,000 (መቶ አስር ሺህ) ኩንታል በላይ መረከቢያ ቦታ በባሌ ሮቤ ከተማ
- በቆሎ (Maize) 10,000 (አስር ሺህ) ኩንታል በላይ መረከቢያ ቦታ ነቀምቴ ከተማ
ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
3. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ምርቱን የሚረከቡበትን የጊዜ ሰሌዳ እና የትራንስፖርት ሁኔታ በግልጽ ማሳወቅ አለባቸው።
5. ለፋብሪካ እና እሴት ለመጨመር /value add/ ለሚያደርጉ ልዩ አስተያዬት ለማድረግ ይረዳ ዘንድ መረጃ ማቅረብ
6. መነሻ ዶክመንት በድርጅቱ ዋና ቢሮ 2000 ብር በመክፍል ተመዝግቦ ሰነዱን መዉሰድ፤
7. የጨረታ አቀራረብ፦ ተጫራቾች የሚገዙትን የምርት ዓይነት፣ መጠን እና የአንድ ኩንታል ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 7 የስራ ቀናት ድረስ በዋና መስሪያ ቤት ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ፣ ቢፍቱህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መጨረሻ ቀን ከሰዓት 8፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ7ኛ ቀን ከሰዓት 8፡30 ይከፈታል።
8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር፦ 0913 812 486
አድራሻ፦ ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ፣ ቢፍቱ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው።
ጉምቢ እህል ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-04-24
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 7 የስራ ቀናት ከሰዓት 8፡00
- Bid opening: 2026-04-24 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 7 የስራ ቀናት ከሰዓት 8፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ጉምቢ እህል ድርጅት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 2,000.00 ብር
- Published: Apr 17, 2026
- Posted at: 2026-04-17T08:28:52.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.