የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር LHR/A/NCD/003/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሚገዛው ዕቃ ተዛማጅ አገልግሎት

  • ሎት 01፡- ኮምፒውተር፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 02፡- የመኪና ኪራይ
  • ሎት 03፡- የቢሮ ማስዋቢያ እቃዎች ምንጣፍ እና መጋረጃን ጨምሮ
  • ሎት 04፡- የመስተንግዶ አገልገሎት ግዥ
  • ሎት 05፡- የደምብ ልብስ

በመሆኑም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1፡ 250,000 ብር/ ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ ለሎት 2፡ 20,000 ሺ ብር /ሀያ ሺ ብር/ ለሎት 3፡ 15,000 ሺ ብር /አስራ አምስት ሺ ብር/ ለሎት 4፡ 5,000 ብር /አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ / CPO/ ወይም ቢድ ቦንድ በመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ከም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ወይም ቢድ ቦንድ በመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ፋይናንስ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም ቴክኒክ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ትክክለኛውን ቅጅ ለየብቻው በፓስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቁት እቃዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀን ቀደም አድርገው ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከተጠቀሰው ቀን ዘግይቶ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም።

6. የጨረታው ፋይናንስ ጎነድ የሚከፈተው እና ግምገማ የሚካሄደው ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተመለከቱት ቴክኒካል መረጃዎች እና የእቃው ናሙናዎች በትከክል ተሟልቶ መቅረባቸው ሲረጋገጥ ነው።

7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

8. በጨረታው አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ የኤጀንሲው የዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት።

9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

10. ተጫራቾች ይህ ማስታቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6.30 እና ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከጎላጎል

11. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰአት ድረስ ከጎላጉል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኝው የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ አጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት 13ኛ ፎቅ ላይ የኤጀንሲው የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት በመምጣት የማይመለስ 300 ብር /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

12. ጨረታው በአደስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኝበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

13. ኤጀንሲው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኝ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጽው መጠን 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

14. ኤጀንሲው የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ : ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኝው የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት 13ኛ ፎቅ ወይም በስልክ ቁጥር 0118 125 085 ደውለው ያነጋግሩ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአደስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-04-29 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአደስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Land Holding Registration and Information Agency
  • Buyer address: ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ኤም.ኤ ህንፃ ግራውንድ ፍሎር የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 17, 2026
  • Posted at: 2026-04-17T08:32:23.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders