የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ማሽነሪዎች ባሉበት ሁኔታ አንድ ላይ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሥርዓት ለአዱኛ ተስፋ የሰጠው የእርሻ መሳሪያ ላይ ተከራዩ የኪራይ ከፍያውን ከባንኩ ጋር በገቡት የካፒታል ዕቃ የዱቤ ግዢና ኪራይ ውል መሠረት ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት ባንኩ የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሸነሪዎች ባሉበት ሁኔታ አንድ ላይ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተከራይ ስም

በጨረታ የሚሸጠው /የሚከራየው ንብረት የሚገኝበት ቦታ

የንብረቱ ዝርዝርና አይነት

 

የጨረታው መነሻ ዋጋ(ብር)

የጨረታው አይነትና ደረጃ

 

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን፣ ሰዓትና ቦታ

1

አዱኛ ተስፋ

ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ ገላን /ከተማ፣ አትላስ ሪዞርት ወረድ  ብሎ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መጋዘን ግቢ ውስጥ፡፡

1.Tractor:- (Brand: CASE IH-FAR- MALL 110JX; Model: TTF 8045.25D.313T; Engine Type: e37: Origion: Turkey: year 2022; Condition: Good) ብዛት 1

2.Disc Plough:- (Brand: OTOMA; Model: O/QD70/E; 4 Discs) ብዛት 1

5,193,750.00

 

2 ዙር ክፍት

ጨረታ

 

ሚያዚያ 29 ቀን 2018 .ከረፋዱ 400-600

ቦታ፡ ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ

 

የጨረታው መመሪያ፣

1. ከላይ የተመለከቱ ንብረቶችን ለመግዛት ወይም ለመከራየት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አካል (ግለሰቦች፣ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) የሀራጁን የመነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25 በመቶ) በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም የተዘጋጀ የባንክ ከፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፤

2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል፤

3. የጨረታው አሸናፊ የንብረቱን የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተ.እ.ታ  (VAT) ጨምሮ ሌሎች ገዢ አንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ ክፍያዎችን የመክፈል ግዴታ አለባቸው፤

4. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች፡

4.1 ቀሪውን ገንዘብ ተ.እ.ታን ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ የጨረታ አሸናፊው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል::

4.2 ንብረቱን ከመረከቡ በፊት በዘርፉ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መበት ማቅረብ ወይም መንግስት ከንብረቶቹ የሚፈለገውን የጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ መክፈል ግዴታ አለበት፡

5. ንብረቱን በባንኩ ማሸነሪ ዱቤ ግዢ እና ከራይ መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች፡

5.1 የባንኩን የማሸነሪ ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆን እንዲሁም ባንኩ በፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት የሚያከናውነው የፕሮጅክት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል፤

5.2 በባንኩ አሰራር መሰረት የሚጠበቅበትን ቅድሚያ ክፍያ በ 15ተከታታይ ቀናት ዉስጥ በመከፈል የባንኩን የማሸነሪ ዱቤ ግዢ እና ኪራይ መስፈርት በማሟላት ዉል መፈረም ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤

6. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ለሐራጁ ያስያዙት ገንዘብ (CPO) በባንኩ ማህተም ተረጋግጦ ይመለስላቸዋል፤

7. ስለ እያንዳንዱ ንብረት ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንጻ 2ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር +251-11-558-6175 /0911-74-35 02 በስራ ሰዓት ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፤

8. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልግ ከደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ጋር በመነጋገር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መመልከት ይችላሉ፡

9. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የካፒታል ዕቃውን ለማስተዳደር ማለትም የመጠለያ ኪራይ፣ የጥበቃ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት፣

10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኦሮሚያ ክልል

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-07
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-05-07 12:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 18, 2026
  • Posted at: 2026-04-18T07:36:06.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders