የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ለ2018/19 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን ማሽነሪዎችን ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች እንዲጓጓዝለት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር (LP/OT/20/SIG/2018
1.የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ለ2018/19 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን ማሽነሪዎችን ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች እንዲጓጓዝለት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ) የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3. ብቁ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ
ጨለለቅ አልሳም ህንጻ ፊት ለፊት
ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 551 6271/500 417፣
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ሚያዚያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡15 ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
7. የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለሰላሳ (30) ቀናት ይሆናል።
8. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
Tender details
- Deadline: 2026-04-28
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-04-28 14:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Sugar Industry Group
- Buyer address: ካሳንቺስ ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ ጆሴፍ ቲቶ መንገድ ከኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሕንፃ በስተጀርባ የሚገኘው 4ኛ ፎቅ ላይ
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 19, 2026
- Posted at: 2026-04-20T07:58:15.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.