የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት የዳቦ መጋገሪያ ማሽነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የመጀመሪያ ዙር የሐራጅ ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ አገልግሎት ግዴታቸውን ካልተወጡ ደንበኛ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና 807/2005 መሰረት የተረከባቸውንና ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን የዳቦ መጋገሪያ ማሽነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

.

የንብረቱ ዝርዝር

ብዛት በቁጥር

የሐራጁ መነሻ ዋጋ

የንብረቱ ሁኔታ

ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

Baking Rotary Oven with Burner Brand: PORLANMAZ, Model: PMDF200, Origin: Turkey

1

10,370,520.53

አዲስ

ግንቦት 13 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 እስከ 600 ሰዓት

2

Mixer

- Brand: PORLANMAZ, Model:

PMSP120, Origin: Turkey

1

 

 

 

3

Dough Divider

Brand: PORLANMAZ, Origin: Turkey

1

 

 

 

4

Dough Moulder Machine

Brand: PORLANMAZ, Model:

PMD350 Origin: Turkey

1

 

 

 

5

Steamer Model: PMCU10, Origin: Turkey

 

 

 

 

6

Trolley with l4tray

-Brand: PORLANMAZ

-Number of pans per trolley --16

- material stainless steel

4

 

 

 

7

Bread Slicer

Brand: PORLANMAZ, Model:

PMBS500, Origin: Turkey

1

 

 

 

8

Sound Proof Generator

Brand: AKSA, Model: AP33,

Rated power: 33KVA

1

 

 

 

የሐራጁ መመሪያ፡-

1. ንብረቱን መግዛት/መከራየት የሚፈልግ ተጫራች የሀራጁን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር 2,074,104.11/ ሁለት ሚሊዮን ሰባ አራት ሺ አንድ መቶ አራት ብር ከ11/100 ሳንቲም/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማቅረብ በሀራጁ መሳተፍ ይችላል፡፡ ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ከንብረቱ የመሸጫ ሂሳብ ላይ ተጫራቹ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ/ የሚቀነስ ይሆናል።

2. ንብረቱ የሚገኘው በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ሃዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ ቱላ ከፍለ ከተማ ዳቶ ቀበሌ ክልል ውስጥ ነው።

3. የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል።

4. ንብረቶቹን ሙሉ በሙሉ በካሽ) በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች የንብረቱ የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥው እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታከስ ክፍያዎችን ጨምሮ ይከፍላል።

5. የሐራጁ አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ የሀራጁ አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ በድጋሚ ይካሄዳል፡፡ ለተሸነፉ ተጫራቾች ለሀራጁ ያስያዙት ገንዘብ ወዲያወኑ ይመለስላቸዋል።

6. ተጫራቹ በከፊል ዱቤ ለመከራየት አሸናፊ ከሆነ ባንኩ ማሸነፉን እንዲያውቅ ካደረገበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ቀሪ ክፍያ አጠቃሎ በመክፈል የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።

7. ሐራጁ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኘበት አድራሻ ይካሄዳል፡፡ በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተወዳዳሪ ሐራጁ በሚካሄድበት ቀን የሐራጁ ሰዓት ከመድረሱ በፊት አንድ ሰዓት ቀድሞ ማለትም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በሐራጁ ቦታ በመገኘት ምዝገባ ማካሄድ፣ ሲፒኦና የታደሰ መታወቂያ ኮፒ ለጨረታው ኮሚቴ ማስረከብ ይኖርበታል።

8. ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 2212 4535 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።

9. ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪከት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።

10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሐራጁ አይገደድም።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-05-21 12:00
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 20%
  • Published: Apr 19, 2026
  • Posted at: 2026-04-20T09:13:23.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders