በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽህፈት ቤት ለወረዳው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አገልግሎቶች እና እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎች ማለትም /ሲሚንቶ፣አሸዋ፣ቆርቆሮ፣ሚስማር የመሳሰሉትን/ ግዥ ፣የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ፣የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸር/ግዥ፣ ለሞ/ወ/ወ/ስፖርት ጽ/ቤት በስፖርት ም/ቤት በጀት የስፖርት ቁሳቁስና ትጥቆች ግዥ፣ለሞ/ወ/ወ/ውሃ ጽ/ቤት በተለያዩ ቀበሌዎች ለሚያስገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታዎች በሙሉ ዋጋ ለማሰራት፣ለሞ/ወ/ወ/ግብርና ጽ/ቤት አይሰራውም መስኖ አውታር ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል ።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
2. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ማግኘት ይቻላል፣
4. ሚገዙትን እቃዎች እና የሚገነቡትን የግንባታ ዓይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/፣ለቢሮ መገልገያ እቃዎች ፈርኒቸር/ 20,000/ሃያ ሽህ ብር/፣ለስፖርት ቁሳቁስና ትጥቆች ግዥ 20,000 / ሃያ ሽህ ብር/ ፣ለሁሉም ግንባታዎች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው፣
6. ለመስኖ ጥገና ግንባታ በዘርፉ የታደሰ ደረጃ 7 እና በላይ የብቃት ማረጋገጫ ፣ ለመጠጥ ውሃ ግንባታዎች በዘርፉ የታደሰ ደረጃ 8 እና በላይ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በዚሁ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡የንፁህ መጠጥ ዉሃ ግንባታዎች፣የአይሰራውም መስኖ አዉታር ጥገና ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በዚሁ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል ሁሉም ጨረታዎች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0116 250 146 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
10. የጨረታ መዝጊያዉ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
አድራሻ፡- አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር (ዋሻ) ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-09
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-05-09 10:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: North Showa Zone Moja And Wedera Wereda Finance Economic Cooperative Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published: Apr 19, 2026
- Posted at: 2026-04-20T09:16:33.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.