Medical equipment and devices

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ-አምስት አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን የአዋላጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፤ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዞን በሚገኛው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከላይ የተገለፁትን አገልግሎቶች መስጠት እንዲችል፣ ልዩ ልዩ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ጨረታው ከሚያዚያ 11፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማክሰኞ ሚያዚያ 20፣2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል::

ተወዳዳሪ ድርጅቶች ዝርዝር የጨረታውን መመሪያ፣ እንዲሁም ግዢ የሚፈፀምባቸውን የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች አይነትና ብዛት የሚገልፀውን ሰነድ፡ የማይመለስ ብር 350.00/ሦስት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የፋይናንስና ግዢ ክፍል መውሰድ ይችላሉ::

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ይህንን ጨረታ በከፊል ወይንም በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::

ተወዳዳሪ ድርጅቶች ጨረታውን በተመለከተ ለሚያስፈልጋቸው ማናቸውም  ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-371-65-44/45/46-የውስጥ መስመር 125/198/199 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ::

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር 011-371-65-44/45/46


Tender details

  • Deadline: 2026-04-27
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ከሚያዚያ 11፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-04-28 14:30
  • Bid opening (note): ሚያዚያ 20፣2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hamlin Fistula Ethiopia
  • Buyer address: Kolfe Keranyo Sub city woreda 09, House number 920 Betel Hospital Street behind Augusta Shirt Factory
  • Bid document price: 350.00 ብር
  • Published on: Reporter (Apr 19, 2026)
  • Posted at: 2026-04-20T11:28:46.000Z
← Back to all tenders