የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ሲሚንቶ፣ የተለያየ ሳይዝ ያለው ብረታ ብረት፣ ብሎኬት፣ ጣውላ፣ ግንዲላ እና የሀበሻ ጽድ እና የጣውላ መቁረጫ ማሽን (ምላጭ)በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ጎ/ገን/ግዥ/ ጨ-1 /212/2018
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለጎንደር ከተማ አስ/ትምህርት መምሪያ ለግንባታ አገልግሎት የሚውል ቁሳቁስ ግዥ እንዲሁም ለጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ለደብረ ብርሀን ስላሴ ቤተክርስቲያን ጥገና አገልግሎት የሚውል ቁሳቁስ ግዥ ማለትም፡-
- በሎት 1 ሲሚንቶ
- በሎት 2 የተለያየ ሳይዝ ያለው ብረታብረት
- በሎት 3 ብሎኬት
- በሎት 4 ጣውላ ፣ግንዲላ እና የሀበሻ ጽድ
- በሎት 5 የጣውላ መቁረጫ ማሽን (ምላጭ)
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-
ማቅረብ የምትችሉት መረጃ፡-
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ
- የግብር መለያ ቁጥር /TIN ያላቸው
- የገንዘብ መጠኑ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የሚገዛውን የቁሳቁስ ግዥ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ /በመክፈል ጎን/ከ/አስ/ ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጎን/ከ/አስ/ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በጎንደር ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ። ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጥሪአችንን አክብረው ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት ይከፈታል። የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ መ/ቤታችን የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።
- ሁሉንም የሚገዙ እቃወች በራሱ ትራንስፖርት ጎ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ/ ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁ 058 126 03 06 ደውሉ መጠየቅ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
P.O box-192 Tele-0581-26-03-06
email- gontipco@ethionet.et
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-04
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-04 10:30
- Bid opening (note): ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Gonder City Administration FEDB
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 19, 2026
- Posted at: 2026-04-20T13:16:57.000Z
Documents
Categories
Building and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksSteel Raw Materials and ProductsSteel, Metals and AluminiumOther MetalsAluminium ProductsWood and Wood WorkingEquipment and AccessoriesMechanicalElectrical, Electromechanical and ElectronicsConstruction Machinery and EquipmentAmharic2merkatoGonder City Administration FEDBAmhara
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.