የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአባላት ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኞችን ማሳተም ይፈልጋል

Description

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር

አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

የአባላት ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ህትመት ጨረታ

ጨረታ ቁጥር 005/2018

1 የመግቢያ እና እጠቃላይ መመሪያዎች

1.1 መግቢያ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽቤት የአባላት ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኞችን ማሳተም ይፈልጋል:: ይህ ሰነድ ተጫራቾች ጨረታ ሰነዳቸውን እንዲያዘጋጁ እና እንዲያቀረቡ የሚያስፈልጉትን መረጃዎች፤ መስፈርቶች እና ቅሶች ይዟል።

1.2 የተጫራቾች ብቃት መሰፈርቶች

በጨረታው ለመሳተፍ የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

  • በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
  •  የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባችሁ
  • የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ግብር የከፈሉበትን ደረሰኝ ማያያዝ፣
  •  ህጋዊ የግብር መለያ ቁጥር ማ.መ.ቁ/ ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ፣
  • በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ክሊራንስ//Tax Clearance/ማቅረብ፣
  • ለተጨማሪ እሴት ታክስ/ተ.አታ/ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

1.3. የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond

  • ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ጋር በማያያዝ የጨረታ ማስከበሪያ(ቢድ ቦንድ)ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የማስከበሪያው መጠን ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ  አጠቃላይ የጨረታ ሁኔታዎች ሁለት በመቶ(2%) መሆን አለበት።
  • ማስከበሪያው በሲፒኦ (CPO) ወይም በባንክ ጋራንቲ መልክ መቅረብ አለበት።
  • የማስከበሪያው ዋስትና ከጨረታ መዝጊያ ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ90 ቀናት የሚሰራ መሆን አለበት።

2፣ ዝርዝር መስፈርቶች እና መጠን /ይዘት

ተ.ቁ

ዓይነት

መለኪያ

 ብዛት

 መጠን

1

የኣባላት ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ

ፖድ

 

6000

15* 20 ኮፒ ብዛት /3/ ዋናው ነጭ 2ተኛው እና 3ተኛው ቢጫ እና ፒንክ ቀለም ሆኖ ባለ 50 ቅጠል

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው የደረሰኝ ህትመቶች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: በተጨማሪም የህትመት ስራውን አጠናቆ ለማቅረብ የሚወሰድባቸውን ጊዜ በግልጽ ማሳየት ይጠበቅባቸል።

3፡ የጨረታ አቀራረብ ሂደት እና ቅጾች

3.1. የጨረታ ሰነደ ዋጋ

  • ይህ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ መልኩ በስምንት መቶ /800/ ብር ይሸጣል።

3.2 የጨረታ አቀራረብ ቀነ ገደብ

  • ተጫራቾቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ሚያዝያ 11 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ ባሉት ተከተታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የመጨረሻ ቀነ ገደብ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል

3.3. የጨረታ አቀራረብ ደረሻ

  • የታሸገ የጨረታ ሰነድ በጉርድ ሾላ ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያ ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባችዋል።

3.4. የጨረታ መክፈቻ

  • ጨረታው ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በዚሁ አዳራሽ /በማኅበሩ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

3.5. የሰነዶች ዝግጅትና ማሸጊያ

ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንታቸውን ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ በፖስታ አሽገው በማዘጋጀት በአንድ ዋና ፖስታ ውስጥ አድርገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

በፖስታው ላይ ተጫራቾች ስምና አድራሻ በግልጸ ማፃፍ ይኖርባቸዋል።

  •  ዋጋው ህትመቱን በድርጅቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድረስ የማድረስ ወጪን ጨምሮ መሆኑን እናረጋግጣለን።

አጠቃላይ የጨረታ ሁኔታዎች ፡-

  • ጥምረት መከልከል፡- አንዱ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተነተርሶ መጫረት / Collusion /በጥብቅ የተከለከለ ነው።

የትዕዛዝ መጠን መቀየር፡- ቅርንጫፍ ጸ/ቤቱ አሸናፊ ተጫራቾችን

  • ያቀረቡትን ዋጋ ሳይቀይሩ በትእዛዙ መጠን እስከ 25% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
  •  የአሸናፊነት መመስረት እና ከክፍያ፡ አሸናፊው ተጫራች የህትመት ደረሰኞችኝ በውሉ መሠረት ካቀረቡ በኋላ በሚቀርቡ የስነድ ማረጋገጫ ክፍያ የሚፈፀመው ህትመቱን ሙሉ በሙሉ ደርሰው ከተረከቡና ተቀባይነት ካገኙ በኋላ ነው።
  • የውል ያለማክበር፡ አሸናፊው ተጫራች ባቀረበው ሰነድ መሠረት ህትመቱን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ / ቢድ ቦንድ/ ለድርጅቱ ገቢ ያደርጋል:: እንዲሁም ተጨማሪ ህጋዊ እርምጃ ሊወስድበት ይችላል።
  • ጨረታውን የመሰረዝ መብት፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዘ መበቱ የተጠበቀ ነው:: ለዚህም ድርጅቱ ምንም አይነት ካሳ የመክፈል ግዴታ የለበትም።

 ተጨማሪ መረጃ -- ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ከታች በተጠቀሰው አድራሻ መገናኘት ትችላላችሁ።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር

አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ሰልክ ቁጥር 011 515 06 08

ፖስታ ሣጥን ቁጥር 41076

አደራሻ፡ ጉርድ ሾላ፣ ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት፣ ድራር ሞል አጠገብ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-29
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-04-29 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Red Cross Society
  • Buyer address: ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ ጉዱ ማይሌ ቀበሌ ከዋና ማ/ቤት ጀርባ በኩል ነው።
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 800.00 ብር
  • Published: Apr 19, 2026
  • Posted at: 2026-04-20T13:40:11.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders