ኬኛ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻና ጠቅላላ ንግድ ኃላፊነቱ የተ/የግል ማህበር ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ አውቶሞቢል እና ሚኒባስ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ
ኬኛ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻና ጠቅላላ ንግድ ኃላፊነቱ የተ/የግል ማህበር ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ እውቶሞቢል እና ሚኒባስ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችልና የመንግስት ግዴታ ስለመወጣቱ የሚያሳይ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታው ሰነድ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ድረስ በቦሌ ጃፖን ኤምባሲ አካባቢ ራማዳ ሆቴል ፊት ለፊት ስንታየሁ በላይ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ባለው ቢሮአችን የፋይናንስ አስተዳደርናንብረት መምሪያ ድረስ በመምጣት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ8ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሺያል እና ቅድመ መገምገሚያዎቹን / ቴክኒክ ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት በፖስታ አሽጐ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ያስገቡበትን 2% ብር ወይም ከቴክኒክ ሰነድ ህጋዊ ሰነዶች ጋር በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው ቀን ዕሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስልክ ቁጥር
0116-14-92-53/0911-74-98-96/0932-12-57-60/ ጃፖን ኤምባሲ አካባቢ
ራማዳ ሆቴል ፊት ለፊት ስንታየሁ በላይ ህንፃ 6ኛ ፎቅ
ኬኛ የግብርና መሣሪያዎች ማምረቻና ጠቅላላ ንግድ ኃላፊነቱ የተ የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-04-27
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ8ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-27 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ8ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kegna Agricultural Equipment Manufacturing and General Trading PLC
- Buyer address: ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ ራማዳ ሆቴል ፊት ለፊት ስንታየሁ በላይ ህንፃ 6ኛ ፎቅ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 19, 2026
- Posted at: 2026-04-20T14:58:05.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.