የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ፑሚስ እና ቀይ አሸዋ ከነትራንስፖርቱ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣
ግንባታና ማማከር ድርጅት በድጋሜ የወጣ ፑሚስ እና ቀይ አሸዋ
ከነትራንስፖርቱ ግዥ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 15/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት ፑሚስ እና ቀይ አሸዋ ከነትራንስፖርቱ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የንግድ ምዝገባ ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5፡00 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 09-13-56-49-36
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-04-30
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30
- Bid opening: 2026-04-30 11:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
- Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
- Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T07:45:59.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.