የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዋናው መስሪያ ቤት ለሚገኙ ቢሮዎች አቅጣጫ ጠቋሚ፣ የህንጻ ብሎክ ቁጥር ጠቋሚ እና የተለያዩ የስራ ማዕረግ (ስታተስ ፕሌት) አቅርቦትና የገጠማ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ፤ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/23/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዋናው መስሪያ ቤት ለሚገኙ ቢሮዎች አቅጣጫ ጠቋሚ፣ የህንጻ ብሎክ ቁጥር ጠቋሚ እና የተለያዩ የስራ ማዕረግ (ስታተስ ፕሌት) አቅርቦትና የገጠማ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ፤ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት(TIN) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድህረ- ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
2. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ በተጫራቹ ድርጅት ስም የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች በዋናው መስሪያ ቤት ለሚገኙ ቢሮዎች አቅጣጫ ጠቋሚ፣ የህንጻ ብሎክ ቁጥር ጠቋሚ እና የተለያዩ የስራ ማዕረግ (ስታተስ ፕሌት) አቅርቦትና ገጠማ ግዥ የቴከኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/23/2018 የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
No. |
የግዥው አይነት / Description |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
|
በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ ቢሮዎች አቅጣጫ ጠቋሚ፣ የህንጻ ብሎክ ቁጥር ጠቋሚ እና የተለያዩ የስራ ማዕረግ (ስታተስ ፕሌት) አቅርቦትና የገጠማ ግዥ |
ብር 84,000.00 (ሰማንያ አራት ሺህ) |
ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
5. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ።
6. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
Tender details
- Deadline: 2026-05-04
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-05-04 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Electric Power
- Bid bond: 84,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T07:48:22.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.