የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ሰመራ ቅ/ጽ/ቤት በሚገኘው ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (የግንባታ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የፈርኒቸር፣ ያገለገሉ ጎማዎች፣ የውሃ እቃዎች፣ ቦንዳዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ዕቃዎችን ለመሸጥ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡_ ሠመራ/ስተአ/001/2018

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ሰመራ ቅ/ጽ/ቤት በሚገኘው ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (የግንባታ እቃዎች፣ የኤሌክክሮኒክስ፣ የፈርኒቸር፣ ያገለገሉ ጎማዎች፣ የውሃ እቃዎች፣ ቦንዳዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የቅ/ፅ/ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈስገ ማንኛውም ተጫራች፡-

1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሸያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰመራ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ቅ/ፅ/ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ከፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከሚያዝያ 12 እስከ ሚያዝያ 23 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።

2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ሰመራ/ቅ/ፅ/ቤት/ Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ማንኛውም ተጫራጭ ከሚያዝያ 12 እስከ ሚያዝያ 23 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ሰመራ በሚገኘው ቅ/ፅ/ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉ።

4. ጨረታው ሰመራ በሚገኘው የቅ/ጽ/ ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሚያዝያ 23 ከቀኑ 5፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

5. የጨረታ አሸናፊ ተጫራቶች ለጨረታው ያሰያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቶች ያሰያዙት የጨረታ ዋሰትና በ3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

6. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።

7. በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጨራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለቅ/ፅ/ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ቅ/ፅ/ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 92 396 6445 ወይም 251 96 601 6656 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልገሎት ሰመራ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-01
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-05-01 15:30
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Refugee and Returnee Service
  • Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 20, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T09:16:02.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders