ሙሉ ጋርመንት የሚያመርታቸውን የተለያዩ የጋርመንት ውጤቶች በግልጽ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ  ማስታወቂያ

ሙሉ ጋርመንት የሚያመርታቸውን የተለያዩ የጋርመንት ውጤቶች በግልጽ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ምርቶች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ጨረታ ላይ የቀረቡ የጋርመንት እቃዎች (አልባሳት ) ዝርዝር

. (No.)

ስም

ብዛት

1

ስትረች ኮተን እጅ ጉርድ ቲሸርቶች በተለያዩ ቀለም

4500 ፍሬ

2

MG እጅ ሙሉ ቲሸርቶች (የአዋቂ የልጆች)

7500/ 600 ፍሬ

3

MG እጅ ጉርድ ቲሸርቶች (የአዋቂ/ የልጆች)

5600 / 350 ፍሬ

4

ቬሎ የልጆች

1000 ፍሬ

5

የወንዶች ቦክሰሮች(ፓንቶች)

19500 ፍሬ

6

የልጆች ኮምፕሌት ቱታዎች በወፍራም በሳይዝ

3000 ፍሬ

7

የተለያዩ ቀለም ያላቸው የማልያ ቲሸርቶች

6200 ፍሬ

8

የልጆች ማልያ ኮምፕሌት

10000 ፍሬ

የጨረታው ቅድመ ሁኔታዎችነና መስፈርቶችን ማሟላት የምትችሉ መሆኑን እንገልፀለን፡፡

  1. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው በ ኤንቨሎፕ በማሸግ በጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ-አርብ 2:30-12:00 እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30-6:00 ሰዓት የማይመለስ 300 ብር በመክፈል ይህ የድርጅታችን የእለት ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ አውቶብስ ተራ ቶት እንጀራ ፊለፊት ዳሽን ባንክ ያለበት ህንፃ አራተኛ ፎቅ በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛትይችላሉ።
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚያወዳድሩባቸው ዕቃዎች 10,000 ብር (አስር ሺህ) ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታ ቦታ አውቶብስ ተራ ቶት እንጀራ ፊ ለፊት ዳሽን ባንክ ያለበት ህንፃ አራተኛ ፎቅ ተጫራቾች( ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ አስረኛው ቀን (10ኛው) ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎችን ናሙና ወደ መጋዘን እየሄዱ መመልከት ይችላሉ።
  6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ11ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ላይ ይከፈታል።
  7. ከላይ ተራ ቁጥር 6 በተገለፀው ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠረው 11ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መክፈቻና መዝጊያው ቀን የሚቀጥለው ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  8. ለጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተገለፀ በ2 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይሆናል። አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል። ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጎ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0962587282/ 0963665618

ሙሉ ጋርመንት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-01
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ11ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-01 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ11ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ሙሉ ጋርመንት
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 20, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T09:21:37.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders