ጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈዉ የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ24/08/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራምእንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች -
4. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለ መሆኑ ከሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክሰ እንቅቃሴያቸዉን ለታክሰ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸዉ የምሰክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
5. ተጫረቾች የጨረታዉን ሰነድ ዘዉትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 24/08/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘትበመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።
6. ለግልጸ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5በመቶ አንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንከ አሰርተዉ በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ተጨራቾች በሚከተለዉ የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።
|
የጨረታ ቦታ |
የጨረታው ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ እና ሐራጅ |
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብነክ የስፖርት እቃዎች፣የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ፣ ፌሮ ብረት፣ቆርቆሮ፣ጥቅል ብረት መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች ጠፍታፋብረት፣የወዳደቁ ብረቶችና ፕላስቲኮች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች፡፡ |
ለግልጽና ለግልጽ ጨረታ በ24/08/2018 እስከ ጠዋቱ 3፡45 |
ግልጽ ጨረታ ለሐራጅ ጨረታ በ24/08/2018 ዓ/ም ጠዋቱ 4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ በ24/08/2018 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡ |
5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸዉ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6. በጨረታዉ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታዉ ዋሰትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸዉ ሲሆን ለተሸናፈ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ዉጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሰራ ቀናት ዉሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. ከአሸናፊ ተ ጫራቾች ማሸነፋቸዉ በደብዳቤ ከተገለጸላቸዉ ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ዉሰጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዉን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።
8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ዉሰጥ ክፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበዉ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታዉ ማሰከበሪያ የሰያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-02
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-05-02 11:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Afar
- Publishing entity: Ethiopian Revenue & Customs Authority Awash Branch
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T09:48:08.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.