በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሸከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 49/2018
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን
- (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፤
- ሞባይሎች ፣ የሞባይል ክፍሎች፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
- የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣
- የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፤
- የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና
- ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆነ እንገልጻለን።
በመሆኑም
1. በተሸከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
2. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ ዕሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለሆነ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
3. በጨረታው ላይ የተሸከርካሪ ወይም የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
4. ተጫራቾች የተሸከርካሪውንና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
5. በዕቃና ተሸከርካሪ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች ወይም ተሸከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ዕ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተዉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼከ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት። ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰነ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
የእቃ ሐራጅ |
እስከ 19/08/2018 |
20/08/2018 4:00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
|
የእቃ ግልፅ |
እስከ 20/08/2018 |
21/08/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል። |
||
|
የተሸከርካሪ ግልጽ |
እስከ 20/08/2018 |
21/08/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል። |
8. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡ አአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
9. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
11. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ዉስጥ ክፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሚ ለሽያጭ ይተካል።
12. መጤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ፡- 011 – 470 - 8503
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወለደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-29
- Bid closing time: 09:45
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-04-29 10:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopia Custom Commission Akakai Kality Custom Branch Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T09:54:35.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.