በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ጤና ቢሮ በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል Diesel Generator በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ጤና ቢሮ በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል Diesel Generator በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀ መስፈርት መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ አግባብና ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኦሪጅናል እና ኮፒ ፣ የመንግሥት አገልግሎት ግዥ በአቅራቢነት ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኦሪጅናልና ኮፒ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፍያ የምስክር ወረቀት TIN number / ኦሪጅናልና ኮፒ በተለይየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- እያንዳንዳቸዉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 /አምሳ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ /RV/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የተጫራቾች ካፒታል መጠን ቢያንስ 3,000,000.00 / ሦስት ሚሊዮን ብር / ብቻ በባንክ ስለመኖሩ የባንከ ስቴትመንት መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በማኖር ዋናዉን ሰነድ በአግባቡ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በግልጽ ኤንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታክስን Nat/ የሚያካትት መሆን አለበት።
- የጨረታው ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በመደበኛ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታላችን ግዥ ንብረት አስተዳዳር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ቀርበዉ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 የጨረታዉ ሳጥን የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0911589226 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ጤና
ቢሮ በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ አርባንጭ
አጠቃላይ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-05-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-06 15:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Arba Minch General Hospital
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 21, 2026
- Posted at: 2026-04-21T10:18:19.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.