የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን የተለያዩ ስራዎችና እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ስራዎችና እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ኦንላይን የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር ለእያንዱንዱ ሎት 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000-70-96 80 882 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን አካውንት ላይ አስገብታችሁ ደረሰኙን ይዛችሁ በመምጣት ሰነዱን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 ማግኘት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ከዚህ በታች በሰንጠረዡ በተገለፀው ምድብ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
|
Lot No. |
Item |
Bid Security |
|
Lot 1 |
Digital Asset Library Development Service |
20,000 |
|
Lot 2 |
Digital Promotion and Content Development |
20,000 |
|
Lot 3 |
Design, Development, and Implementation of a Smart Digital information center |
20,000 |
|
Lot 4 |
Digital Screen |
20,000 |
|
Lot 5 |
Television |
20,000 |
4. ተጫራቾች የመወዳዳሪያ ሀሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን በየሎቱ በመከፋፈል ቴክኒካል ኦሪጅናል ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
5. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
6. በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በሚገኙበት ጨረታው በወጣው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 4፡15 ሰዓት 7ኛ ፎቅ በሚገኘው በኮሚሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
8. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አራዳ ክ/ከተማ፣ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጎን፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ ቁ. 251-011-1-25-07-33
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን
Tender details
- Deadline: 2026-05-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-01 10:15
- Bid opening (note): ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን
- Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Apr 21, 2026
- Posted at: 2026-04-21T10:28:22.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.