በአብክመ ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የግብአት አቅርቦትና መካ/የውል እርሻ አስ/ቡድን ለመስኖ አት/ፍራ ዉሀ አጠቃቀም ቡድን አገልግሎት የሚውሉ የአቡካዶ ዘር እና የቡና ዘር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2018
በአብክመ ግብርና ቢሮ የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የግብአት አቅርቦትና መካ/የውል እርሻ አስ/ቡድን ለመስኖ አት/ፍራ ዉሀ አጠቃቀም ቡድን አገልግሎት የሚውሉ የአቡካዶ ዘር እና የቡና ዘር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
3. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1 - 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ኦሪጅናል በሚወዳደሩበት ተቋም ስም ማስያዝ አለባቸው።
8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግብርና መምሪያዉ የግብአት አቅርቦት እና ስርጭት ገጠ/ፋይ የስራ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 4፡01 ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የጨረታ የመወዳደሪያ ሰነድ ማለት የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)፣ በዘርፉ እና የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣የማቅረቢያ ቦታ፣ የማቅረቢያ ጊዜ፣ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀን ይሆናል፡፡
9. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ በሰ ሜን ጎጃም ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 08 በመቅረብ ዘወትር በሥ ራ ሠዓት መውሰድ ይችላሉ ፡፡
10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና መምሪያዉ የግብአት አቅርቦት እና ስርጭት የስራ ቡድን ቢሮ በ11ኛዉ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡ በ11ኛው ቀን ህዝባዊ መንግስታዊ እና ከመንግስት የስራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል ወይም በስልክ
13. ቁጥር 09 12 76 42 43/09 23 89 92 89 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-04-30
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛዉ ቀን 4፡01 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-30 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛዉ ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: North Gojam Zone Agricultural Command
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T10:36:00.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.