የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እና የሕንፃ መሣሪያ ዕቃዎች (ላፕቶፕ፣ ዴስክቶፐ፣ ፕሪንተር፣ እስካነር፣ ቴሌቪዥን፣ ፍሪጅ፣ ሞንታርቦ፣ ኤሲ፣ ሚስማሮች፣ ብረቶች እና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎች) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ዕቃዎችን ለመሸጥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- ጋምቤላ/ ስተአ/002/2018

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እና የሕንፃ መሣሪያ ዕቃዎች (ላፕቶፕ፣ ዴስክቶፐ፣ ፕሪንተር፣ እስካነር፣ ቴሌቪዥን፣ ፍሪጅ፣ ሞንታርቦ፣ ኤሲ፣ ሚስማሮች፣ ብረቶች እና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡

1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጋምቤላ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ከፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከሚያዝያ 13/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።

2. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugee and Returnee Service/ በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ማንኛውም ተጫራች ከሚያዝያ 13 እስከ ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል፡፡ ቅዳሜና እሁድ የሥራ ቀናት አይደሉም።

4. ጨረታው ጋምቤላ በሚገኘው የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሚያዝያ 26/2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

5. የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

6. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።

7.በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአግልግሎት መሥሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8.አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር +251 911 278 481 ወይም +251 910 464 495 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-05-04 10:30
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: የስደተኞችና ተመላሾች አገልገሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 21, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T11:22:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders