የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ የመኪና አይነቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 05/2018

የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ የመኪና አይነቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልግ ተጫራች ሁሉ ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅራቢዎች የተመዘገቡ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ለሚችሉ ሁሉ ክፍት ነው።

2. ተጫራቾች የመኪናዎቹን ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሆኖ የሚያቀርቡትን የመኪና ስፔስፊኬሽን የሚገልጽ ዝርዝር መግለጫ ካታሎግ በቴክኒካል ፖስታው ውስጥ አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢ.ቁ 03 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /C.PO/ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የቴክኒካሉን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ ፋይናንሻሉን ሲፒኦውን ጨምሮ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ ለየብቻ በመለየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡30 /ሰዓት/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 05 በይፋ ይከፈታል። ሆኖም እለቱ የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የጨረታ ሰነዱን 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ከጠዋቱ 4፡30 / ሰዓት/ በይፋ ይከፈታል።

8. ለተጨማሪ ማብራሪያ ኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስ.ቁ 033-551-0272 በመደወል ወይም በግንባር በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።

9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኮምቦልቻ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-06
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 /ሰዓት/
  • Bid opening: 2026-05-06 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡30 /ሰዓት/
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Kombolcha City Water Supply and Sewerage Service
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Apr 21, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T11:33:19.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders