የአማራ ህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማከፋፈያ ማዕከል የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች እና የተሽከርካሪ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የአማራ ህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማከፋፈያ ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ክፍሎች አገልግሎት የሚዉሉ

  •  ሎት 1. የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 3. የኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  • ሎት 4. የቢሮ ዕቃዎች እና
  • ሎት 5. የተሽከርካሪ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደስ እና በዘርፋ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3.  ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች 1 ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ውድድሩ በሎት ስለሆነ ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት አለባቸዉ፡፡
  6. ስለ ጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ ከፍሎ በመዉሰድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሥራ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 3 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በማዕከሉ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅጽ መሰረት የነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በመሙላትና በየገጹ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በዚሁ እለት 11፡30 ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ቢሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ማዕከሉ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
  12. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 04 15 ወይም 058 320 19 92 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058 320 30 88 በመላክ መጠየቅና ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡ ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጎን ባሕር ዳር
የአማራ ህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማከፋፈያ ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-05-04
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት 11፡00 ድረስ
  • Bid opening: 2026-05-05 09:30
  • Bid opening (note): ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: አማራ ህክምና ኦክስጅን ማምረቻ ማከፋፈያ ማዕከል
  • Bid bond: 3%
  • Bid document price: 50.00 ብር
  • Published: Apr 20, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T11:45:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders