በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የግዥ ንብ/አስ/ቡድን የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎቶች መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የግዥ ንብ/አስ/ቡድን
- ሎት 1. የእነ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የህፃናት ማቆያ እና ሰነድ ክፍል የG+3 ግንባታ በደረጃ GC/BC 6 እና በላይ የሆነ ሙሉ ማሽነሪውን እና የሰው ሃይል ራሱን ችሎ የሚሰራ፣
- ሎት 2. የኮንስትራክሽን ማቴሪያል እቃዎች፣
- ሎት 3. የስፖርት ትጥቆች እና እቃዎች፣
- ሎት 4. የደንብ ልብስ፣
- ሎት 5. የውጭ ሀገር ፈርኒቸር እቃዎች ለሁለተኛ ጊዜ፣
- ሎት 6. የኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣
ሎት 7. የጽዳት እቃዎች፣ - ሎት 8 የኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና ለሁለተኛ ጊዜ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለሎት 1. ማንኛውም ተቋራጭ የታደስ የግንባታ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ እና ተቋራጮች ለግንባታ አገልግሎት የሚያስፈልገውን የሰው ሀይል እና እቃዎች ማቴሪያሎች /ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦ መስራት የሚችሉ ለሁሉም ሎት መ/ቤቱ ከጨታው አሸናፊ ላይ 3 በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል ምንም አይነት የግንባታ ስራ ካልሰራ ላለመሰራቱ ከሚመለከተው መ/ቤት ደብዳቤ ማስጻፍ አለበት፡፡
- ለሎት 1. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ ከመሃንዲስ ግምት 25 በመቶ በታች ካልሆነ አጠቃላይ ከተወዳደሩበት 10 በመቶ የባንክ በጥሬ ገንዘብ ፣በሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ሲኖርበት ከተዘጋጀው የመሃንዲስ ግምት ዋጋ አንፃር የተጋነነ ዝቅተኛ ከ25 በመቶ ዝቅ ብሎ ካቀረበ ለውል ማስከበሪያ 25 በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡
- ለሎት 1. በጨረታ የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ወይም ተቋራጭ ዝርዝር የግንባታ ዋጋ (cost breakdown) እና የግንባታ መርሃ ግብር (project workschwettle) እንዲሁም ባቀረበው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ (conformation letter) አሸናፊነቱ
በተገለጸ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህን ማድረግ ካልቻለ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ - ለሎት 1. ከተዘጋጀው የመሃንዲስ ግምት ዋጋ አንፃር የተጋነነ ዝቅተኛ ከ25 በመቶ ዝቅ ብሎ በመግዛት አሸናፊ ሆነው የሚመረጡ የግንባታ ተቋራጮች ውል ይዘው ወደ ስራ ሲገቡ የቅድሚያ ክፍያ እንደማይፈቀድ መታወቅ አለበት፡፡
- ለሎት 1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ ከሎት 2. እስከ ሎት 7. ለእያንዳንዳቸው ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለሎት 8. ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ፋይናንስ ቡድን ግዥ መግዛት ይችላሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን ማስረጃ እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ይታወቅ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ለሎት 1 ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) ለሎት 2. ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ ከሎት 3 እስከ 8 ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ እንዲሁም ከሎት 2 እስከ ሎት 8. ላሉ ግዥዎች አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን በኋላ ለውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ ገንዘቡን በመ/ቤታችን መሂ 1 ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ለሎት 1 ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ31ኛው ቀን ከሎት 2 እስከ 8 ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኝም የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ለተላለፈው ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን እሁድ ቅዳሜ እና የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ፖስታ ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያውን በመጨመር ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ድርጅት ውል በሚያዝበት ወቅት እነማይ ወረዳ ዐቃቢ ህግ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡ ለሎት 1. ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የተሞላው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ከሎት 2. እስክ 8. ለእቃዎች የተሞላው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ግዚ ለ40 ቀናት ይሆናል፡፡
- ለሎት 1. አሸናፊ የሆነው ተጫራች በራሱ ወጭ በእንግሊዘኛ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ እና የመሀንዲስ ግምት ከህጋዊ ትርጉም ቤቶች ወደ አማርኛ ማስተርጎም ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የሚሰራው የግንባታ ስራ ከG+1 ጀምሮ እስከ G+3 መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅትኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቾች አጠቃላይ የስራ ዝርዝር እና ዲዛይን ከሰነዱ ጋር አብሮ የተያያዘ መሆኑን እንዲታት፣ ለሎት 1. በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ እንዲሁም ፓራፍ ያደረገም ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ በጨረታ ስነዱ በዋጋ መሙያው እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ማህተም ስምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡ ለሎት 2 ከጨረታ ሰነዱ ላይ በማየት የአባይ አሸዋ በየቀበሌው የሚራገፍ መሆነ መታወቅ አለበት፡፡
- ከሎት 2 እስከ 8 በባለሙያ የሚረጋግጡ እቃዎች በባለመያ እየተረጋገጡ የምንረክብ መሆኑን እና አሸናፊው ተጫራች የአሸነፈውን እቃ እነማይ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ሥር ባለው ንብረት ክፍል ድረስ አስፈላገውን ወጭ በመሸፈን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- ከሎት 2 እስከ 8 ላሉ የሎት ምድቦች መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጨረታ ይዘት ሣይቀይር ከእቃው ጠቅላላ መጠን ላይ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታ ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 01 00 /08 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
እነማይ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-05
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-05 10:00
- Bid opening (note): በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Enemay Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T11:52:00.000Z
Documents
Categories
Building ConstructionConstruction and Water WorksConstruction Machinery and EquipmentSport Materials and EquipmentShoes and Other Leather ProductsTextile, Garment and LeatherTextile, Garments and UniformsOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureCleaning and Janitorial Equipment and ServiceOffice Machines and ComputersMaintenance and RepairOthersFinishig WorksEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesAmharic2merkatoEnemay Woreda FEDBAmhara
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.