የአዲስ አቦባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶች ግዥ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ቸ/ቁ 19/2018

የአዲስ አቦባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ከታች በሎት የተዘረዘሩትን ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የተለያዩ ብረታ ብረቶች
  • ሎት 2 ማርብል እና ሴራሚክ
  • ሎት 3 አልሙኒየም ፕሮፋይሎች ከነአክሰሰሪው
  • ሎት 4 የጣሪያ ቆርቆሮ እና ተያያዥ የግንባታ ግብዓቶች
  • ሎት 5 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
  • ሎት 6 የግርግዳ ቀለሞች

ስለሆነም

1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር

  • ለሎት 1፡ 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ)
  • ለሎት 2 ፡200,000 (ሁለት መቶ ሺህ)
  • ለሎት 3፡ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ)
  • ለሎት 4 100,000 (አንድ መቶ ሺህ)
  • ለሎት 5፡ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ)
  • ለሎት 6 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ረፋድ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ 5፡00 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  • አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ
  • ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ስልክ ቁጥር 09-13-56-49-36/ 09 11-15-60-36

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-02
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ረፋድ 4፡30
  • Bid opening: 2026-05-02 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ረፋድ 5፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
  • Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 21, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T12:10:19.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders