ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ መለዋዎጫዎች እና ግብአቶች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ግልጽ ጨረታ ቁጥር WSSF/LP/003/2026

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መለዋዎጫዎች እና ግብአቶች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ምድብ

የእቃው አይነት

1

ELECTROMECHANICAL ITEMS (MECHANICAL ITEMS, ELECTRICAL ITEMS, BEARINGS, ELECTRODES)

2

FIRE RESISTANCE CEMENTS, HEAT RESISTANCE BRICKS, DIFFERENT CIVIL WORK MATERIALS

3

AGROCHEMICALS, AGRICULTURAL TOOLS (FIELD EQUIPMENTS)

4

DIFFERENT FACTORY GENERAL USE MATERIALS, GRINDING, DRILLING AND PLASMA CUTTING MACHINES, DIFFERENT PASTES, PAINTS AND OILS, DIFFERENT OIL SEALS, ELECTRODES

5

DIFFERENT GENERAL ITEMS FOR FIELD EQUIPMENTS MAINTENANCE DIVISION (METALS, BEARINGS, SEALS AND AUTO ELECTRIC GENERAL.....) AND OTHERS.

6

FACTORY ELECTRICAL ITEMS (LIGHTING and MAINTENANCE MATERIALS, EXHAUST FAN MOTORS AND PANEL, ACCESSORIES FOR FIBRIZERS, SEMATIC CARDS, ENAMELED COPPER WIRE, WELDING CABLES, CABLE LUG, CABLE JOINT and others.

 

1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ለእያንዳንዱ ምድብ ለየብቻ የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000473232708 በጨረታ ተሳታፊው ድርጅት ስም ገቢ በማድረግ ከላይ በተጠቀሱት ግዢዎች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

ወንጂ /ሸዋ ስኳር ፋብሪካ

ሜክሲኮ ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201

ለተጨማሪ መረጃ 011 558 5229/ 011 551 6082/ 09 68 48 24 45 አዲስ አበባ

2. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ቴክኒካ ዶክመንት ጋር የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የታክስ ክሊራንስ ሰርትፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፊኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በየግዢ መጠይቁ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 6፡00 ከመሆኑ በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

4. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተገለጸው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 201 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚሆን ሲሆን ትክክለኛው ቀን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚጠቀስ ይሆናል።

5. ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-06
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-06 13:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 7፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Wonji Shoa Sugar Factory
  • Buyer address: ፊሊፕስ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 301
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Apr 22, 2026
  • Posted at: 2026-04-22T08:36:22.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders