በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት የቁም ደን ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በደ/ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያና ተሁለደሬ ወረዳዎች በተለያዩ ቀበሌዎች በተለያዩ የመንግሥት ደኖዎች 13,015.70 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድና ነጭ ባህርዛፍ ቁም ደን፣ ደ/ጎንደር ዞን ጉና በጌምድር ወረዳ አርጋ ድድም ቀበሌ ዋልጋሜዳ የመንግስት ደን ውስጥ 3,980 47 ሜ/ኩብ የፈ/ዕድ፣ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ሰራቆ እና እያሆ ሰረባ ቀበሌዎች አንጎባና አባ ጎልጃ የመንግሰት ደን ውስጥ 1571.43 ሜ/ከብ የፈ/ጽድ እና 671.41 ሜ/ኩብ ነጭ ባህርዛፍ ቁም ድን፤ በሰ ሸዋ ዞን ባሶና ወረና ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በተለያዩ የመንግስት ደኖች ውስጥ በድምሩ 23,068.93 ሜ/ኩብ የነጭ ባህር ዛፍ ቁም ደን ምዕ/ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ ተረር የመንግሥት ደን ውስጥ 3446.3926 ሜ/ኩብ ቀይ ባህርዛፍ ቁም ደን እና አዊ ዞን ባንጃ ወረዳ እረዕ ተበሌ በተርያ የመንግስት ደን ውስጥ 16412.5 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን በድምሩ 46724.17 ሜ/ኩብ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች:-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተእታ(VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ለጨረታ የቀረበውን ቁም ደን ምርቶች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ስዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
  4. የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ት/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን ምርቶች በኦሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነድ ላይ ማህትም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች « የቁም ደን ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከወጣበት ቀን (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ እስከ መጨረሻ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡ዐዐ ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይሁን እንጅ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፣ ሆኖም አሸናፊው ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል።
  8. ተጫራቾች ቅልቅል ተብሎ የቀረበውን እና በሎት የቀረበውን ቁም ደን ሁሉንም ከፍልፋይ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  9. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  10. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- ባህ/ዳር 058 226 3095፣ ደ/ታቦር 058 441 0306፣ ደ/ብርሃን 011 637 5017፤ እንጅባራ 058 227 0485፣ ደ ማርቆስ 058 871 9004፣ ኮ/ቻ 09 14 71 66 36 ደውሉ መጠየቅ ይችላል።

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 የስራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-02 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 የስራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Forest Enterprise
  • Buyer address: ባህር ዳር ቀበሌ 14 አረጋውያን ህንፃ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 22, 2026
  • Posted at: 2026-04-22T08:41:54.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders