የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የተለያዩ የስፖርት ዕቃዎች ግዢ

Description

በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ድ/ዳ/አስ/ወ/ስ/ኮ/መደበኛ/01/2018

መ/ቤታችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን

ሎት አንድ የተለያዩ የስፖርት ዕቃዎች ግዢ

በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በመስኩ የተሰማሩ አቅራቢዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ በብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በድሬደዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር 11 የመወዳደሪያ ዋጋ የያዘውን ሰነድ በመውስድ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው በግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው ለመሳተፍ፤

  • የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የታደስ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ክሪላንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት/ እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ/ቢድ ቦንድ/ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • አንዱ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ በፐርሰንት ተንተርሶ ዋጋ መቀነስም ሆነ መጨመር አይቻልም።
  • በጨረታው አሸናፊዎች ከተገለፀ በኋላ በ7 ቀን ጊዜ ውስጥ ቀርበው ውል ባይፈፅሙና የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ያሸነፉት ዋጋ 10% በመስያዝ ውል ባያገቡ የጨረታ አሸናፊነታቸው ተሰርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ የሚወረስ ይሆናል
  • ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። ጨረታው በወጣ በ 16ኛው ቀን ማለትም በቀን 28/8/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ በ3፡00 ላይ ታሽጎ በዛኑ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬደዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ከሚገኘው ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 11 የሚከፈት ይሆናል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ

በስልክ ቁጥሮች፡- 09 15 03 80 55 / 09 13 81 73 02 በስራ ሰአት ደውሎ መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-05-06
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-05-06 09:30
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Diredawa Administration Youth and Sport Comission
  • Bid bond: 150,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 22, 2026
  • Posted at: 2026-04-22T08:45:14.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders