Sports, tents and camping equipment

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የስፖርት ቁሳቁስና ትጥቅ ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር – 07/2018

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ከዚህ በታች የተመለከቱትን የስፖርት ቁሳቁስና ትጥቅ ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ( TIN ) ያላቸው ፣
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 ( ሁለት መቶ ሺህ ብር ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT ) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የስፖርት ቁሳቁስና ትጥቅ ግዥው የፍላጎት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው ሳምፕል” መሠረት የሚቀርብ መሆን ይኖርበታል።
  6. የግዥ ፈጻሚው መ/ቤት የቫት ክፍያ ላይ 7.5% እና ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ደግሞ 3% ቀንሶ የሚያስቀር ይሆናል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በመምሪያው የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ ማግኘት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በማስያዝ ደረሰኙን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሽገው በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰሜን ሽዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡01 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
  11. የግዥ ፈጻሚ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመገኘት በፋክስ ቁጥር 011-681-27-36 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 011-681-32-41 / 011-681-63-96 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ

ደ/ብርሃን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-15
  • Bid closing time: 10:01
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡01 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-15 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shewa Zone Finance and Economic Development Office
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (May 31, 2026)
  • Posted at: 2026-06-02T07:12:56.000Z
← Back to all tenders