ተስፋ ብርሃን ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት የእርባታ በጎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የእርባታ በጎች
ግዥ ጨረታ
ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ለሚገኙ የእንሰሳት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ አርሶ አደር ቤተሰቦች በድጋፍ መልክ የሚሰጡ የእርባታ በጎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ማህበራት፣ ድርጅቶች ወይም ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፎቹ የተሠማራችሁና በጨረታዉ ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-
- በበጀት ዓመቱ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸሁ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ቲን ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸሁ፣
- በእንስሳት አቅራቢነት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ማህበራት፣ ድርጅቶች ወይም ነጋዴዎች
ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) ቀናት የጨረታ ሠነዱን በብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ቀይት ከሚገኙ የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በመግዛት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 1% ከባንክ ሲፒኦ ጋር በፖስታ አሽጎ በማስገባት እንድትወዳደሩ እየጋበዝን ጨረታዉ በ11ኛዉ ቀን በ5፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ5፡30 ሠዓት የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን 11ኛዉ ቀን በካላንደር የሚዘጋ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳዉቃለን።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ተስፋ ብርሃን ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
ደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር
ጣይቱ ክፍለ ከተማ
ቀይት ቀበሌ
ለተጨማሪ መረጃ
ስ.ቁ 011-656-0249 ወይም
ኢሜል፡ procurement@tesfab.org
Tender details
- Deadline: 2026-05-02
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): ጨረታዉ በ11ኛዉ ቀን በ5፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-05-02 11:30
- Bid opening (note): ጨረታዉ በ11ኛዉ ቀን በ5፡30 ሠዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: ተስፋ ብርሃን የበጎ አድራጎት ማህበር
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 22, 2026
- Posted at: 2026-04-22T12:04:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.