በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ የመገልገያ ቁሳቁሶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በሪስቶር ፕሮጀክት በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች የእንስሳት ሃብት አገልግሎት መልሶ ማቋቋም ድጋፍ ለሦስት ዘር አምራቾች ማህበራት እና ለሦስት የእንስሳት መኖ ዘር አምራቾች ኢንተርፕራይዝ የተለያዩአይነት የመስሪያ ቁሳቁሶችን በሪስቶር ፕሮጀክት በጀት ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የመገልገያ ቁሳቁሶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ቁጥር እሀልማቢሮ 133/2018 የእንስሳት መኖ ዘር አምራች ማህበራት እና ኢንተርፕራይዝ የመገልገያ ቁሳቁስ ግዥ፣
|
የእቃው ዝርዝር |
|
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የሚገዙ ግብዓቶች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላለ።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 103374.00 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ በሚገኘው የአብክመ ግብርና ቢሮ ቁጥር 69 የማይመለስ ብር 400.00 / አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- የመወዳደሪያ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሰረት በእያንዳንዱ እቃ ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል።
- ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና የዋጋ ማቅረቢያ/ፋይናሻል ፕሮፖዛል እያንዳንዱን ለየብቻው ታሽጐ መቅረብ ይኖርበታል፤
- ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ መታሸግ ያለባቸው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ከፋይነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማስረጃ፣ የመጫረቻ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀናት፣ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በስንት ቀን ውስጥ እቃውን አጠቃሎ ማስረከብ ያለበት መሆኑን የሚገልጽ ጽሁፍ፤
- ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ ማሸግ ያለብዎት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብቻ ነው።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 4516 /058 220 6479 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይከፈታል፣ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 058 220 4516 ወይንም 058 220 6479
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-08
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-08 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara National Regional State Livestock and Fisheries Resource Development Bureau
- Bid bond: 103374.00 ብር
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published: Apr 23, 2026
- Posted at: 2026-04-23T09:30:24.000Z
Documents
Categories
Tents and Camping EquipmentPackaging and LabellingTest & Measurement ToolsMachinery and EquipmentAgriculture and FarmingHand Tools and Workshop EquipmentTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsMechanicalAmharic2merkatoAmhara National Regional State Livestock and Fisheries Resource Development BureauAmhara
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.