የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ፣ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የግልፅ እና የሀራጅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ
- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ የቤት ማስዋቢያ ፤
- የቤት ዕቃ ኮንስትራክሽን፣
- አልባሳት፤
- እስፔርፓርት
- የፅዳት ዕቃ፣
- ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ጨረታ የቀረቡትን እቃዎች 20/08/2018 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅጽ ቤቱ ይገልፃል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች –
- በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ በመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
- ለሀራጁ ጨረታው 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤
- ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ(5%) ሲፒኦ C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤
- ለሀራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
- ለግልፅ ጨረታ ቅጽ ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
- ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃ ክፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤
- እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
- በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
- ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፣
- ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወሰድም፤
- ተጫራች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከቀን 20/08/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ22/08/2018 ዓ.ም 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
- ሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው 22/8/2018 ከጠዋቱ 4፡15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤
NB፦ አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም።
የጅግጅጋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-30
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: Apr 23, 2026
Categories
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesHome Appliance and SuppliesFurniture and FurnishingTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsSpare Parts and Car Decoration MaterialsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceOffice FurnitureHouse FurnitureOther SalesSales, Disposals and ForeclosureFood and BeverageFood Items and DrinksBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksAmharic2merkatoEthiopian Customs CommissionSomali
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.