የሲር ለና በጎ አድራጎት ድርጅት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መግዛት ይፈልጋል

Description

መኪና ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ለየሲር ለና በጎ አድራጎት ድርጅት በኢትዮጵያ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በምዝገባ ቁጥር 4979 ተመዝግቦ በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ወላጅ አጥ ህጻናት ተኮር የሆኑ የልማት እና የሰብአዊ ድጋፍ ዙሪያ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን የራሱን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ በጽ/ቤቱ ለሚሰጠው አገልግሎት እና የሰብአዊ ድጋፍ ስራ የሚውል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም

  1. በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያለው
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
  3. ክፍያ እንደተፈጸመ ወዲያውኑ መኪናውን ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን/የመኪናውን ስፔሲፊኬሽን ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ከተጫረቱበት ዋጋ በላይ ዋጋ መጨመር አይችሉም።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በተሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በሚታሰብ 5 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

 ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ጳውሎስ ሆስፒታል ጀርባ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት አጠገብ።

ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ስልክ ቁጥር፡-09-12-49-00-06 / 09 78 99-99-59

የሲር ለና በጎ አድራጎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-28
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በሚታሰብ 5 ቀናት ውስጥ
  • Bid opening: 2026-04-28 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የሲር ለና የበጎ አድራጎት ድርጅት
  • Published: Apr 24, 2026
  • Posted at: 2026-04-24T07:01:20.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders