የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን እና ለምርጫ ሚውሉ ሚስጥራዊ ሰነዶችን ሚስጥራዊነታቸውን በጠበቀ መልኩ ፈጭተው መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ የሃገር ውስጥ ፋብሪካዎች በሽያጭ በማስተላለፍ ለማስወገድ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን እና ለምርጫ ሚውሉ ሚስጥራዊ ሰነዶችን ሚስጥራዊነታቸውን በጠበቀ መልኩ ፈጭተው መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ የሃገር ውስጥ ፋብሪካዎች በሽያጭ በማስተላለፍ ለማስወገድ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፦
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ፋብሪካዎች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከመዘጋቱ በፊት ባሉ ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 በሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦርዱ ንብረት አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 506 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተገለፁ የቴክኒክ መገምገሚያ መስፈርት እና የፋይናንስ ፕሮፖዛላቸውን በተለያዩ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብም ሆነ ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም። በተጨማሪም አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀ የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ የህትመት ውጤቶቹን የአንድ ኪሎ ነጠላ ዋጋ እና እንዲሁም በተጠቀሰው አጠቃላይ የክብደት መጠን ጠቅላላ ዋጋን በግልፅ በመሙላት ስም እና ፊርማቸውን ከታች ማስፈር አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ለጨረታው ማስከበርያ ዋስትና ይሆን ዘንድ ብር፡ 100,000.00 /መቶ ሺህ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ CPO በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስም አሰርተው ከመጫረቻ የቴከኒክ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ በ8.00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦርዱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። በጨረታው መክፈቻ ላይ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
- ተጫራቾች የራሳቸው የሆነ አገልግሎት የሰጡ ወረቀቶችን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ፋብሪካ ያላቸው ስለመሆኑ የአወጋገድ ስነስርዓቱ ላይ የቦርዱ የስራ ኃላፊዎች የፖለቲካ ፓርቲ ታዛቢዎች እና መገናኛ ብዙሃን እንዲገኙ እና ሂደቱን እንዲዘግቡ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በሽያጭ እንዲወገዱ የቀረቡትን የህትመት ውጤቶች እና የምርጫ ሚስጥራዊ ሰነዶች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከመዘጋቱ በፊት ባሉ ተከታታይ የስራ ቀናት ሳሪስ ቡና ቦርድ ፊት ለፊት በሚገኘው የቦርዱ ስልጠና ማዕከል እና መልካ ቃሊቲ ግቢ ባሉ መጋዘኖች በመገኘት በአካል መመልከት ይችላሉ።
- ቦርዱ ሌላ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 551 0252 ወይም ቦሌ መንገድ ከፍላሚጎ ገባ ብሎ ባለው የቦርዱ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-05-05
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-05-05 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian National Election Board
- Buyer address: ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 24, 2026
- Posted at: 2026-04-24T07:05:56.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.