በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የኤሌክትሪክ መኪናዎች ኪራይ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 14/2018

በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለቂርቆስ ከ/ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ መኪናዎች ኪራይ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡- በኤሌከትሪክ የሚሰራ ሚኒባስ
  • ሎት 2፡- በኤሌክትሪክ የሚሰራ የቤት መኪና አውቶ ሞቢል

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/tin no/ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ሰርተፊኬት ያለቸው።
  2. ለሚወዳደሩባቸው አገልግሎት ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00/ ሃምሳ ሺህ/ በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  3. የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል ፣1 ቴከኒካል ሰነድ ኮፒ፣1 ፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናል እና 1 የፋይናንሽያል ሰነድ ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም 1 ሲፒኦ ለብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
  4. የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኘው የቂርቆስ ከፍለከተማ አስተዳደር ህንፃ 9ኛ ፎቅ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ የስራ ቀን በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደ ማሳሰቢያ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊትለፊት የቂርቆስ ክፍለከተማ

አስተዳደር 9ኛ ፎቅ ስልክ 0115548264 /0118-69-43-66

የቂርቆስ ክ/ከ/አስተዳደር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-05 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published: Apr 24, 2026
  • Posted at: 2026-04-24T07:33:18.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders