በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 007/2018

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከዚህ በታች የተገለፁትን ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

No.

Items

Quantity

1

Double cabin pick up

2

2

Station wagon 9 seat hard top

2

3

Meat transporter van truck

2

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

4. የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት/Tin Number/ ያላቸው።

5. ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።

6. ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፈቃዱን በማቅረብ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ሆሳዕና በሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የማይመለስ 500.00/አምስት መቶ/ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

7. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት አየር ላይ ይውላል።

8. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 20ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9. ጨረታው አየር ላይ መቆያው ጊዜ ባበቃበት ቀን 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

10. ጨረታው በጋዜጣ የሚውልበት የመጨረሻ ቀን በዓል፣ ቅዳሜ ወይም እሑድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።

11. ተጫራቾች 600,000/ስድስት መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።

12. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0910 928 986 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት

/ሆሳዕና/

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-13
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 20ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-13 14:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Central Ethiopia Regional Finance Office
  • Bid bond: 600,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 24, 2026
  • Posted at: 2026-04-24T07:42:54.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders