የድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለት/ቤቱ ቋሚ ዕቃዎች፣ ልዩልዩ መሳሪያዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ከእነ እጅ ዋጋ፣ የሰራተኞች ካፌ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የዕቃ ግዢ
ጨረታ ማስታወቂያ
የድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለት/ቤቱ ቋሚ ዕቃዎች፣ ልዩልዩ መሳሪያዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ከእነ እጅ ዋጋ፣ የሰራተኞች ካፌ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመወዳደር የሚችሉት
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
- የዘመኑን ግብር የከፈለ
- የአቅራቢነት ሊስት ተመዝጋቢ የሆነ
- QR code ደረሰኝ ተጠቃሚ የሆነ
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 12 በግንባር በመገኘት የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ። ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ማስከበሪያ ለሎት 6313 (ቋሚ እቃ) እና ሎት 6241 (ለመኪና ዕቃዎች) ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በ2% የተሰላ ሲሆን ለሎት 6219 (ልዩ ልዩ ዕቃዎች) ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር) በ2% የተሰላ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃዎች ናሙና /ሳንፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የመሸጫ ዋጋውን እና ፎቶ ኮፒውን በተለያዩ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አዘጋጅቶ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 12 ውስጥ በግንባር በመገኘት ማስገባት ይኖርበታል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 12 ውስጥ የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- አሸናፊው ተጫራች የአሸነፈበትን እቃ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ውስጥ ድረስ በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርበታል።
- ለካፌ ተጫራቾች መንግስት ባስቀመጠው በየተቋሙ ገቢዎች አነስተኛ ነጋዴዎችን በሚመለከት ባወጣው መመሪያ መሰረት እንቀበላለን።
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ለአነስተኛ እና ጥቃቅን መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት በሚፈቀድላቸው ዘርፍ ብቻ እንዲሳተፉ እናበረታታለን።
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ ወደ ሰባተኛ በሚወስደው መንገድ 50 ሜትር ላይ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር 011-277-5609/10 011-868-5356
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-06
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-06 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Dilachn Secondary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published: Apr 25, 2026
- Posted at: 2026-04-25T08:51:25.000Z
Documents
Categories
Spare Parts and Car Decoration MaterialsCatering and Cafeteria ServicesConsumable GoodsMaterialsEducation and TrainingWood and Wood WorkingMetal and Metal WorkingEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesAmharic2merkatoDilachn Secondary SchoolAddis Ababa
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.