የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባህርዛፍ ግንድ ጉዶበረት ቀበሌ ቶራ መስክ አካባቢ ደን ሳይት እና አባሞቴ ቀበሌ እምቧጭ ጉር አካባቢ ደን ሳይት ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሽን የጠረጋ ስራ ማሰራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው
Description
በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባህርዛፍ ግንድ ጉዶበረት ቀበሌ ቶራ መስክ አካባቢ ደን ሳይት እና አባሞቴ ቀበሌ እምቧጭ ጉር አካባቢ ደን ሳይት ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሽን የጠረጋ ስራ ማሰራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ማሽኑን ሎት 1 ጉዶበረት ቀበሌ ቶራ መስክ አካባቢ ደን ሳይት ለ150 ሰዓት እና ሎት 2 አባሞቴ ቀበሌ እምቧጭ ጉር አካባቢ ደን ሳይት ለ100 ሰዓት አጠቃላይ ለ250 በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፡-
1. በዘርፉ የተሰማራና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
3. የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 – 3 የተጠቀሱትና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሎት 1 20,000.00/ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 2 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
6. አሸናፊው ድርጅት ማሽኑን በራሱ ወጪ ስራው የሚሰራበት ጫካ ድረስ የማድረስና ስራውን ሲጨርስ የመመለስ ግዴታ አለበት፣ እንዲሁም የራሱ ኦፕሬተር ሊኖረው ይገባል፡፡ የኦፕሬተር ሰርቪስ ተጫራቹ ማቅረብ አለበት።
7. የአንዱ ሳይት ሥራ ሲጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ሳይት ማሽኑን የማዘዋወር ኃላፊነት የአከራዩ ድርጅት ኃላፊነት ነው።
8 አሸናፊ ተጫራች በስራ ቦታ ላይ ከነዳጅ ወጪ በስተቀር የኤክስካቫተሩን የዘይት፣ ቅባት፡ ግሪስ፣ ሰርቪስ ቀላልና ከባድ ጥገናዎች፣ የጎማ ጥገናና ግዢ፣ የሹፌር ደመወዝ እና አበል እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን በራሳቸው ይሸፍናሉ።
9. ማሸኑ በስራ ላይ እያለ ቢበላሽ አሸናፊው ተጫራች በራሱ ወጪ የተበላሸውን የማስተካከል ስራ የሚሰራ ሲሆን በቀላሉ ማስተካከል የማይችል ከሆነ በራሱ ወጪ አንስቶ በምትኩ ሌላ ማሽን የማስገባት ግዴታ አለባቸው።
10.ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለበት።
11. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፣
12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
13. ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።
14 የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ላይ ወይም እሁድ ከዋለ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
15 አሽናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሽነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል።
16.ተራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሁለቱም ሎቶች በአንድ ላይ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከካምፓኒው ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
17.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0910 368 437 ደውለው ይጠይቁ
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00
- Bid opening: 2026-05-11 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Debrhe Berhan Wood Processing P.L.C
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 25, 2026
- Posted at: 2026-04-25T10:02:59.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.