ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ለገማድሮ ቡና እርሻ ልማት የእንግዳ እና የሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ ሥራ የጉልበት ወይም የሙያ የአገልግሎት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EAC 030/2018

1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ለገማድሮ ቡና እርሻ ልማት የእንግዳ እና የሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ ሥራ የጉልበት ወይም የሙያ የአገልግሎት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -11፡00 ሰዓት ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3.ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-

  • አንድ ዋና /Original የጨረታ ሰነድ ለብቻው በታሸገ ፖስታ።
  • አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ እንዲሁም።
  • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
  • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የእንግዳ እና የሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታን ስራ የጉልበት ወይም የሙያ የአገልግሎት ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም ኮንዲሽናል ባንክ ጋራንት ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ በሮ ቁጥር 208 ሲሆን፤ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል።

6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ያልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።

7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 667 6204 ፋክስ ቁጥር 011 673 2006 ደውለው መጠቀም ይችላሉ።

8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-05-12 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio Agri-CEFT Pvt.Ltd.Co.
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 26, 2026
  • Posted at: 2026-04-27T09:56:41.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders