በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለሚገነባዉ G+3 አስተዳደር ህንፃ ለበርና እና ለመስኮት መስሪያ አገልግሎት የሚውል የጣዉላ፣ የእምነበረድ፣ የጅፕሰም እና የቀለም ጨረታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት አማካኝነት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳዉ ለሚገነባዉ G+3 አስተዳደር ህንፃ ለበርና እና ለመስኮት መስሪያ አገልግሎት የሚውል የጣዉላ፣ የእምነበረድ፣ የጅፕሰም እና የቀለም ጨረታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ያላቸው።
  3. ከ200,000/ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት።
  4. ለመንግሥት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችል።
  5. ተጫራቾች ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና ሌላም መረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በሁለት ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ዕቃዎች ዝርዝር |እስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይችላሉ።
  7. መ/ቤቱ ካስቀመጠው ውጭ በራሱ ጊዜ እስፔስፍኬሽን የጨመረና የቀነሰ ወይም ያስቀመጠ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
  8. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በዝ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እና በ16ኛው ቀን 2፡30-6፡00 በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት በዚያው ቀን 8፡ዐዐ ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በዝ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግልፅ ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /በሲ.ፒ.ኦ/ማስያዝ አለበት።
  10. ተጫራቾች ከሚወዳደሩበት ሰነድ ላይ ከአንዱ ዋጋው እና ጠቅላላ ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ያደረገ ከጨረታው ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ
  11. ተጨራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ የአንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ የሚለውን በጥንቃቄ ለያይተው መሙላት አለባቸው።
  12. ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆኑ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት።
  13. ተቋሙ በጨረታው ዙሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግስት ሥራ ዝግ ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን ና ሰዓት በተመሳሳይ ጊዜ ይከፈታል።
  15. ማንኛውም ተጫራች ከኦርጅናል ሰነዱ ላይ የንግድ ፍቃዱን ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ የማያስገባ ወይም ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ ሳያስገባ ውጭ ላይ የተወ ከውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን ይታወቅ።
  16. የጨረታ አሸናፊው አካል ውል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ቀጥታ በአስቸኳይ በውሉ መሰረት ንብረቱን ዝ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት።
  17. ለበለጠ መረጃ 033 462 0050/53/49 ደውሎ መጠበቅ ይቻላል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-11
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2፡30-6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-11 14:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Zekuala Woreda FEDB
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 26, 2026
  • Posted at: 2026-04-27T09:59:03.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders