የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር እና ላፕቶፕ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተርና ላፕቶፕ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ጨረታውን እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደለ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ወልቂጤ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ቀርበው የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ስም ተዘጋጅቶ ከሚያቀርቡት ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር በተናጠል ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎችን ማለትም አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በጥንቃቄ በተናጥል በታሸገ ፖስታ እንዲሁም አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል አንድ ኮፒ በተናጥል በታሸገ ፖስታ በመለየት ሁሉንም በጥንቃቄ በታሸገ እና ፖስታ በማሸግ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል።
5. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያውኑ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት በፕሬዝዳንቱ ቢሮ በይፋ ይከፈታል።ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በተገለፀው ሠዓት ይከፈታል።
6. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሑድ ወይም የሕዝብ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሠዓት ይሆናል።
7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሠነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አደራሻቸውንና የደንብን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
8. በሚቀርበው ሠነድ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 13 68 85 66 / 09 33 14 01 35 / 09 11 06 61 57 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-06
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-06 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Gurage Zone High Court
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 26, 2026
- Posted at: 2026-04-27T10:03:20.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.