አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር ሸቀጥና ሸቀጥ ነክ ያልሆኑ ልዩ ልዩ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር ሸቀጥና ሽቀጥ ነክ ያልሆኑ ልዩ ልዩ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የዚህን ጨረታ ሰነድ በተገለፀው አድራሻ በመግዛት ማንኛውም ተወዳድሮ ያሸነፈው አካል እቃዎቹን መግዛት የሚችል ሲሆን:-

1. የጨረታ አይነት፡ የውሃ ፓምፕና መለዋወጫ፣ ጄነሬተርናመለዋወጫዎች፣የመኪና ጎማ ፣ካመነዳሪ፣ፍላፕ ፣የመኪና ባትሪ፣ኮፒውተር፣ ፕሪንተር ስልክና ሌሎች ተያያዥ ዕቃዎች፤ አገልግሎት የማይሰጡ በፀሃይ የሚሰሩ ፋኖሶች ፣መለዋወጫዎች አገልግሎት የማይሰጡ የቢሮ እቃዎች፣የቢሮና የፅህፈት መሳሪያዎች እጣን የተለያዩ ብረታ ብርቶች፣ ወኪንግ ትራክተር አገልግሎት የማይሰጡ ልዩ ልዩ የጥራጥሬ ማበጠሪያ ማሽነሪዎች፣ ልዩ ልዩ እቃዎች በሚል በተለዩት የጨረታ ሰነዶች በጥቅል (በሎት/ LOT) አደራጅቶ ገዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ነው፤

2. ማንኛውም ተጫራች (የተፈጥሮም ይሁን ሕጋዊ ሰውነት ያለው) በአንድ የጨረታ ሎት /Lot/አይነት ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ ገዝቶና ሞልቶ ማስገባት አይችልም:: ሆኖም ሻጭ ለሽያጭ ባወጣቸው የተለያዩ ሎቶች ላይ በሁሉም ላይ በመሳተፍ ዋጋ ማቅረብ ይችላል::እያንዳንዱ ተጫራች በተመሳሳይ ሎት (በአንድ ሎት) ላይ ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ ሞልቶ ማቅረቡ ከተረጋገጠ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።

3. ሻጭ ይህንን ጨረታ ሰነድ በመሸጡ ምክንያት በማንኛውም ሁኔታ የውል ስምምነት እንዲፈጽም አያስገድደውም:: የውል ስምምነት እንደያዘም አይቆጠርም።

4. ተጫራቾች ለመግዛት ዋጋ የሰጡበትን የንብረት አይነት ወይም የሎት አይነት ጠቅላላ ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ዋጋ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች በኩባንያው ዋና መ/ቤት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በአቅራቢያው በሚገኘው ሻጭ አድራሻ ማለትም አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ከሚገኘው አምባሰል ንግድ ስራዎች ድርጀት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 503 ፣በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ ዜጋ ለመሆናቸው ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ወይም ፓስ ፖርት ኮፒ እንዲሁም የንግድ ድርጅቶች ከሆኑ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

7. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከታወጀበት እለት 18/08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ማለትም በ05/09/2018 ከቀኑ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ይታሸጋል:: የኩባንያው ንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ በእለቱ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በሻጭ አድራሻ ማለትም አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ከሚገኘው አምባሰል ህንጻ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 305 የጨረታ ሰነድ የመከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: በጨረታ ሰነድ የመከፈት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታውን ዋጋ አያሳጣውም።

8. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ለሚያወጡት የትኛውም ዓይነት ወጭ (በጨረታው ተሳትፎ ቢያሸንፍ፣ ቢሸነፍ፣ በተለያየ ምክንያት ከጨረታው ውጭ ቢደረግ ወይም ጨረታው ቢሰረዝ) ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም።

9. በጨረታ ሰነዶቹ ላይ ማብራሪያ የሚፈልግ ተጫራች በዚህ የጨረታ ሰነድ ላይ በተመለከተው የሻጭ አድራሻ የሚፈልገውን ማብራሪያ በፅሑፍ መጠየቅ ይችላል።

10.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ያለባቸው ከሻጭ ብቻ ነው:: ተጫራቾቹ የጨረታ ሰነዱን በቀጥታ ከሻጭ ካለማግኘታቸው ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ማንኛውም ዓይነት ጉድለት ወይም አለመሟላት ሻጩ ተጠያቂ አይሆንም።

11.ሻጭ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር

ስልክ ቁጥር 011460701748 / 0114 700 751


Tender details

  • Deadline: 2026-05-13
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-05-13 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ambasel Trading House PLC
  • Buyer TIN: 0000018284
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 26, 2026
  • Posted at: 2026-04-27T10:20:37.000Z
  • Buyer website: https://www.ambaseltrading.com/

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders