ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የድርጅታችን ንብረት የሆነውን አፍሪካ ህብረት አካባቢ የሚገኝ ህንፃ የሴፕቲክ ታንክ ስላብ ሥራ ማከናወን ደረጃ 5 እና በላይ የሚችሉ የግንባታ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

CN/NCB/32/2018

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የድርጅታችን ንብረት የሆነውን አፍሪካ ህብረት አካባቢ የሚገኝ ህንፃ የሴፕቲክ ታንክ ስላብ ሥራ ማከናወን ደረጃ 5 እና በላይ የሚችሉ የግንባታ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም የግንባታ ሥራውን የምታከናውኑበት ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-10፡30) ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ

ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 011-156 9992

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Apr 26, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders