Business and factory foreclosure
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ንብረቶች በልዩ ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በልዩ ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረት አድራሻ
|
የንብረት ዝርዝር
|
የቦታ ስፋት (በሄክታር)
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)
|
የጨረታ ሁኔታ
|
የጨረታ ደረጃ
|
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
አቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም
|
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስ/ላ/ ክ/ከተማ ወረዳ 08
|
ጋቴፕሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፤ የህንፃ ግንባታዎች የኤሌክትሪክ ስራዎች፣ማሽነሪዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፣ የጥሬ ዕቃና የምርት ክምችት |
1,678 ካሬሜትር በሊዝ የተገኘ መሬት
|
122,600,997.28 (አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሃያ ስምንት ሳንቲም)
|
ልዩ ድርድር
|
አንደኛ
|
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋት 4፡00-6፡00 ሰዓት
|
ማሳሰቢያ፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ሆኖ ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ በማስገባት ከ4፡00-6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ቀርበው መደራደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ባንኩ ያስያዘውን ገንዘብ ይወርሳል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ታወር ሁለት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል። ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
- አንዳንድ የድርጅቶች ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ፤ታክስ ለመክፈል ይገደዳል።
- ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ንብረቱን መጎብኘት ይችላሉ።
- ባንኩ ንብረቱን የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል:።
- የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ያሳወቃል። ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ የማስፈፀም ሃላፊነት አለበት።
- በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።
- በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-5373/ 011-524-4269 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። የመያዣ ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልግ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
Tender details
- Deadline: 2026-05-26
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-05-26 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Reporter (Apr 26, 2026)
- Posted at: 2026-04-27T13:18:26.000Z