በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የፋይበር ኦፕቲክስ መስመር ዝርጋታ ስራ በግልፅ ጨረታ በዘርፉ የተሰማሩ ሙያተኞችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 5/2026

በከልቻ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የፋይበር ኦፕቲክስ መስመር ዝርጋታ ስራ ለማሰራት በግልፅ ጨረታ በዘርፉ የተሰማሩ ሙያተኞችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

  1. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 04/05/2026እ.ኤ.አ ወይም 26/08/2018 ዓ.ም ድረስ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡30 ሰዓት አዳማ ሶደሬ መንገድ በሚገኘው የአ/ማህበሩ ዋና መ/ቤት ወይም አዲስ አበባ ካዲስኮ ሕንጻ ፊት ለፊት በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
  2. መስመሩ የሚዘረጋበትን ስፍራ አዳማ በሚገኘው ዋናው መ/ቤታችን በግንባር ቀርበው በመመልከት እናየአ/ማህበራችንን አይሲቲ ባለሙያዎች በማነጋገር መረጃ ማግኘት ይቻላል።
  3. ጥራት ያለው እቃ በማቅረብ የሚሰሩበትን የእጅ እናየእቃ ዋጋ ከጨረታ ማስከበሪያ የብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ ብር) CPO በማስራት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ተመሳሳይ ስራ የሰራችሁበትን የስራ ልምድ እና የመልካም ስራ አፈፃጸም ማስረጃችሁን በማደራጀት ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ፕሮፖዛላችሁን በተለያዩ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱንም በአንድ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የድርጅታችሁን ማህተም በማተም ጨረታውበሚከፈትበት እለት በአዳማ ከተማ በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤታችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን እ.ኤ.አ በ06/05/2026 ወይም በ28/08/2018ዓ.ም ከ4፡30 እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ እንድታስገቡ፣
  4.  የጨረታው ሳጥን በ8፡05 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ በ8፡30 ይከፈታል።
  5. አ/ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ - በስልክ ቁጥር 0221-11 17 91 /0913- 09 10 03 አዳማ 0114 42 27 11 ወይም 0114-43 13 48 አዲስ አበባ ይደውሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-05-06
  • Publishing entity: Bekelcha Transport Share Company
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Apr 26, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders