ፀደይ ባንክ አ.ማ. የቢሮ መጠቀሚያ ዕቃዎች (Office Equipment) እንዲሁም የካውንተር ስራ ለአንድ አመት ቋሚ ውል በመያዝ ለማሰራት ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ /ጨ/00013/2018
ፀደይ ባንክ አማ ከስር በሰንጠረዥ የተገለፁትን የቢሮ መጠቀሚያ ዕቃዎች (Office Equipment) እንዲሁም የካውንተር ስራ ለአንድ አመት ቋሚ ውል በመያዝ ለማሰራት ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት-1 -- የቢሮ መጠቀሚያ ዕቃዎች (Office Equipment)
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
ብዛት |
|
1 |
Fire Resistant Cash Safe Big |
60 |
|
2 |
Fire Extinguisher |
30 |
|
3 |
Metal Detector |
100 |
ሎት-2 ፡- የካውንተር ስራ ለአንድ አመት ቋሚ ውል በመያዝ ለማስራት
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት ነጋዴ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።
1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደስ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ በጨረታ ለመካፈል ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ክሊራንስ ሊኖራቸዉ ይገባል።
2. ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክመንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ የ90ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል። ከየትኛውም የፀደይ ባንክ ኢማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።
4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ስነዱን መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
6. የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።
7. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 558 1658
ፀደይ ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published: Apr 26, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.