በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የእንስሳት መድሃኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለቀወት ወረዳ እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ተ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የእንስሳት መድሃኒት
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
- በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የግዥው መጠን ከብር 200000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ከ1-4 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታው ውድድሩ በጥቅል መሆኑን አውቀው ጨረታውን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ በተገለጸው በሎት የሚወዳደሩ ተጫራቾች ብር 20000 (ሀያ ሺህ ብር) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ በተገለጸው በሎት የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሰነዱ ጸንቶ ከሚቆይበት 40 ቀን በኋላ በተጨማሪ 20 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቀው የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- በሎትı ተወዳድረው የሚያሸንፉ ተጫራቾች 10% የውጩ ማስከበሪያ በማስያዝ መዋዋል የሚጠበቅባቸው ሲሆን አቅርቦቱን ላከናወኑበት ክፍያ ሲጠይቁ በስማቸው የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይጠበቁባቸዋል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ በተገለጸው በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል:: ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 033-664-16-12 ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን
በቀወት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-12 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Kewet Woreda Finance Office
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Apr 27, 2026
- Posted at: 2026-04-28T07:16:02.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.