የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
Description
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OFWE/GU-16/2018
ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ገ/ድዴሳ፤ ያዮ፤ ሲቦ ቶሊ ቆቦ እና ገ/ዲማ ዲስትሪክቶች፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጋራ ሙለታ ዲስትሪክት፤ ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት መጋዳ፤ ቦሬ፤ ዋዳራ እና አዶላ ድስትሪክቶች ፤ ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ሆሮ ጉዱሩ፤ ምዕራብ ወለጋ፤ ቄለም ወለጋ እና ምስራቅ ወለጋ ድስትሪክቶች ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ የ" Grevillea robusta " እና የ"Pinus" ግንድላ እንዲሁም በነዚሁ ድስትሪክቶች ላይ የዝርያዎች ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ሲቦ ቶሌ ቆቦ ዲስትሪክት፤ አርሲ ቅ/ጽ/ቤት አዳባ ዶዶላ ዲስትሪከት፤ጂማ ቅ/ጽ/ቤት በለጠ ጌራ ድስትሪክት እና ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት ቦሬ ድስትሪክት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ የ "Grevillea robusta እና የ"Pinus" ግንድላ እንዲሁም በነዚሁ ድስትርክቶች ላይ የዝርያዎች ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
1. የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና "TIN number” ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 2ዐዐ /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ጅማ ከተማ፤ አርሲ ት/ጽ/ቤት ነጌሌ አርሲ ከተማ፤ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጭሮ ከተማ፤ ቦራና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት አዶላ ከተማ እና ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ጊምቢ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት ይቆያል።
3. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፋትበት ትክክለኛዉ ቀንና ሰዓት በጨረታዉ ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች፤ በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO)ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
5. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 240 249 በመደወል ማጠየቅ ወይም " www.oromiaforest.et ድህረ ገፅ ማጎብኘት ይችላሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-05-11
- Publishing entity: Oromia Forest and Wildlife Enterprise
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published: Apr 27, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.