የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ኤሌክትሪክ ሚኒባስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 010-2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ኤሌክትሪክ ሚኒባስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው የአገልግሎት ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ (cpo) መጠን |
ምርመራ |
|
1 |
የመኪና ኪራይ |
10,000.00 |
|
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ቲን /Tin/ ሰርተፊኬት እና ክሊራንስ ማስረጃ እንዲሁም ሶስተኛ ወገን፣ ቦሎ እና ኢንሹራንስ የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ተሽከርካሪ ጥራትና ቁመና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት ተቋማችን በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት የፋይናንስ ሰነድ ከመከፈቱ በፊት አቅርበው በጥራት ኮሚቴ ቴክኒክ ምርመራ የሚካሄድ ይሆናል፤
3. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ ህንጻ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-04 ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት 10ኛ ፎቅ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10-08 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለውድድር የሚቀርበው የቴክኒክ ሰነድ እንዲሁም የዋጋ/ፋይናንሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል።
5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ስም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ 10ኛ ፎቅ እንገኛለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911 002 020 / 0913 727 549
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-08
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Plan and Development Bureau
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 27, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.